ትውልድ የሚያሻግር የጸጥታ መዋቅር መገንባት ወቅቱ የሚጠይቀው ተግባር ነው።

13
የሰሜን ሸዋ ዞን እና የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር “በጀግንነት መጠበቅ፣ በሰብዓዊነት ማገልገል!” በሚል መሪ መልዕክት ለጸጥታ አባላት ሲሰጡ የነበረው ሥልጠና ተጠናቅቋል።
በሥልጠና ማጠናቀቂያ መርሐግብሩ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኀላፊ እሸቱ የሱፍ (ዶ.ር) ሠልጣኝ ተመራቂዎች የክልሉን ሰላም እና ጸጥታ በማረጋገጥ እና ለሀገራዊ ግዳጅ ሁልጊዜም ዝግጁ በመኾን አለኝታነታቸውን ማሳየት ይገባቸዋል ነው ያሉት።
ተመራቂዎቹ በጽኑ ሥነ-ምግባር ለሕዝብ ከለላ እና መከታ በመኾን ሀገርን የሚያጸኑ ጀግኖች እንደሚኾኑ ያላቸውን ዕምነት ገልጸዋል።
በሀገር መከላከያ ሠራዊት የ112ኛ ኮማንዶ ክፍለ ጦር አዛዥ ኮሎኔል አደራጀው ሰረበ ትውልድ የሚያሻግር የጸጥታ መዋቅር መገንባት ወቅቱ የሚጠይቀው ተግባር መኾኑን ተናግረዋል።
ሀገሩን የሚወድ፣ ታማኝ እና ለወገኑ ራሱን አሳልፎ የሚሰጥ ሠራዊት መገንባት እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል።
የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ በድሉ ውብሸት የጸጥታ መዋቅሩ በጽናት እና በትጋት የሕግ የበላይነትን ብሎም ሰላምን በማረጋገጥ በልማት ሥራዎች ላይ ማተኮር እንደሚገባም አሳስበዋል።
የሰሜን ሸዋ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ኤልያስ አበበ ትናንት ጀግኖች አርበኞች ያጸኗትን ሀገር የበለጸገች በማድረግ ለመጭው ትውልድ ማስረከብ እንደሚገባ ጠቁመዋል።
ለዚህም የጸጥታ መዋቅሩ አስፈላጊው ቁርጠኝነት ሊኖረው እንደሚገባም አስገንዝበዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous article“ከትላንት ተምረን፣ ዛሬን በአግባቡ በመጠቀም የተሻለ ነገን መገንባት ይገባል” ጋዜጠኛ ሙሉቀን ሰጥዬ
Next articleለስልታዊ ቡድኖች የሚቀርቡ አጀንዳዎች እየተጠናቀቁ ነው፡፡