
መንግስት በቅርቡ ‘ መሶብ ‘ የተሰኘ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እንደ ሀገር የተንዛዛ አገልግሎት አሰጣጥን በመቀየር በተለይም 117 ዓመታት በቆየው የሲቪል ሰርቪስ አገልግሎት አሰጣጡ ላይ ከጊዜ፣ ከወጪ እና ከእንግልት አንፃር የነበረውን ከፍተኛ ችግር እረፍትና መፍትሔ የሰጠ ነው።
መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት በአንድ ጣራ ስር የተለያዩ የመንግስት አገልግሎቶችን በማጣመር ምርጥ የዲጂታል ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የሚሰጥ አገልግሎት ነው። የአሠራር ሥርአቱ ዜጎች የተሟላ የዲጂታል አማራጮችን በመጠቀም በቀላሉ የተለያዩ የፌደራል ተቋማትን አገልግሎት እንዲያገኙ ያስችላል። ይህም ባለጉዳዮች ወደ ተለያዩ ቢሮዎች የሚያደርጉትን ምልልስ፣ ረጅም የወረፋ ጥበቃ እና ከወረቀት ጋር ተዛማጅ የሆኑ ሥራዎችን የሚያስቀር ነው፡፡
መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት የመንግሥት ተቋማትን አገልግሎቶች በአንድ ጣራ ስር እና በዲጂታል ቴክኖሎጂ በማቀናጀት ለዜጎች ፈጣን፣ ግልጽ እና ምቹ አገልግሎት የሚሰጥ ዘመናዊ ሥርዓት ነው። ይህ ማዕከል ዜጎች ከተለያዩ ተቋማት የሚፈልጓቸውን ጉዳዮች ለመጨረስ ከአንድ ቢሮ ወደ ሌላ ቢሮ የሚዞሩበትን እንግልት እና የቢሮክራሲ ሰንሰለት ሙሉ በሙሉ ያስቀራል።
መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ዋና ዋና ጥቅሞችና ባሕሪያት፦
✨ ጊዜና የገንዘብ ብክነትን መቀነስ፦ ባለጉዳዮች በተለያዩ ቢሮዎች መካከል የሚያደርጉትን ምልልስ እና ረጅም ሰዓት የሰነድ ጥበቃን ያስቀራል።
✨ ዲጂታላይዝድ አሠራር፦ አገልግሎቱ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የታገዘና ከወረቀት ንክኪ ነጻ የሆነ በመሆኑ ግልጽነትን ያረጋግጣል።
✨ ብልሹ አሠራርን መዋጋት፦ የዜጎችንና የሠራተኞችን ቀጥታ ግንኙነት በመቀነስ የሙስና ዕድሎችን ያጠባል።
✨ አካታችነት፦ ለአረጋውያን፣ ለአካል ጉዳተኞች እና ለእናቶች ልዩ ምቾችን (ለምሳሌ የሕፃናት ማቆያ) ያካተተ ሰብአዊ አሰራር አለው። መረጃው የአማራ ክልል ሲቪል ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ቢሮ።
#AMECO #mesob #Ethiopia🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ሐምሌ_28_2018_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
