“የአረንጓዴ አሻራ ርብርቡ ልዩ ትርጉም አለው” አቶ አሸተ ደምለው

8

 

ሲከናወን የዋለው የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር የዞኑን ነጻነት በማጽናት ረገድ ከፍተኛ ትርጉም እንዳለው በአማራ ክልል የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን አሥተዳደር አስታውቋል።

በዞኑ ቃብትያ ሁመራ ወረዳ “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪቃል የአንድ ጀንበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ተከናውኗል።

በፕሮግራሙ ላይ የዞኑ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች፣ የሀገር መከላያከያ ሠራዊት ከፍተኛ አዛዦች እና ልዩ ልዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል።

የዞኑ ዋና አሥተዳዳሪ አሸተ ደምለው ያለፉት ዓመታት የሕወሃት መዋቅር የተነቀለበት እና የዞኑ ሕዝብ ነጻነቱን ያረጋገጠበት ነው ብለዋል።

ኅብረተሰቡ ከልማት ተሳትፎው ጎን ለጎን ያገኘውን ነጻነት ለማጽናት በንቃት እንዲሳተፍም መልዕክት አስተላልፈዋል።

የተተከሉ ችግኞችን መንከባከብ እና በአካባቢው ያለውን ደን መጠበቅ እንደሚገባ ያሳሰቡት ደግሞ የቃብትያ ሁመራ ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ ክብረአብ ስማቸው ናቸው።

ዛሬ ላይ የሚተከለው ችግኝ ለሰው ልጅ ሕይዎት እና ለተስተካከለ ሥነ ምህዳር ወሳኝ ተግባር መኾኑን ያነሱት ደግሞ የዞኑ ግብርና መምሪያ ኀላፊ አወቀ መብራቱ ናቸው።

ወይዘሮ ጌጡ በቃብትያ ሁመራ ወረዳ የፈረስ መግሪያ ቀበሌ ነዋሪ ናቸው። መንገዳቸው ለህክምና ወደ ሆስፒታል ቢኾንም ችግኝ ሳይተክሉ ማለፍ እንዳልፈለጉ አጫውተውናል።
አቶ ደጀን ሽፈራው ደግሞ የአንባደርኩታን ቀበሌ ነዋሪ ሲኾኑ ዛሬ የሚተከለው ችግኝ ለነገው ትውልድ ተስፋ እና ምሳሌ መኾኑን ገልጸዋል።

የችግኝ ተከላው በቀሪ የክረምት ወራትም ተጠናክሮ የሚቀጥል ሲኾን ከዚህ ጎን ለጎን ማኅበረሰቡ አካባቢውን በንቃት እንዲጠብቅ ተመላክቷል።

#AMECO #greenlegacy #Ethiopia

#ሁመራ #ሐምሌ_27_2018_ዓ_ም

ዘጋቢ:- አምሳሉ አሞኘ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article“ከሚተከሉት ችግኞች ከ60 በመቶ በላይ የሚኾኑት ለምግብነት የሚያገለግሉ ናቸው” አቶ አዲሱ አረጋ
Next articleበትንንሽ እጆች ትልልቅ አሻራዎች !