
የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ በሰጡት መግለጫ እንደገለጹት ሕዝቡ የመሪውን ጥሪ ሰምቶ ከጫፍ ጫፍ በመነቃነቅ ከጠዋቱ 12:00 ጀምሮ በስፋት እየተከለ ይገኛል ነው ያሉት።
ዛሬ ኢትዮጵያን በላባቸው እና በጉልበታቸው የራሳቸውን ደማቅ ታሪክ እየጻፉ ነው ብለዋል። እስከ 10:30 በተደረገው እንቅስቃሴ 765ነጥብ 7 ሚሊዮን ወይም 96 በመቶ ችግኞችን መትከል ችለናል ነው ያሉት። 24 ነጥብ 7 ሚሊዮን ሕዝብ መሳተፉንም አብራርተዋል።
ይህም 378 ሺህ ሄክታር መሬት ተጨማሪ ደን እንዲሸፈን ያደረገ ስለመኾኑም አብራርተዋል። የአፈር መሸርሸርን የሚገታ ታሪክ የተሠራበት ነው ብለዋል።
ከሚተከሉት ችግኞች ከ60 በመቶ በላይ የሚኾኑት ለምግብነት የሚያገለግሉ ስለመኾናቸውም ተናግረዋል።
ዛሬ የተከልነው ለነገ ምግብ ነው ያሉት ሚኒስትሩ የውጭ ምንዛሬን የሚያመጡ ስለመኾናቸውም አመላክተዋል።
ለወጣቶች፣ ለአርሶ አደሮች እና አርብቶ አደሮች ተጨማሪ ገቢ የሚያመነጩ እና ለኑሮ መሠረት የሚኾኑ ናቸው ብለዋል። በቀሪ ሰዓታት የያዝነውን ዕቅድ ለማሳካት ርብርብ ማድረግ እንደሚያስፈልግም ጥሪ አቅርበዋል።
#AMECO #greenlegacy #Ethiopia🌱🇪🇹
#ባሕር_ዳር #ሐምሌ_27_2018_ዓ_ም
ዘጋቢ:- አሰፋ ልጥገበው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
