“በክልሉ አረንጓዴ ዐሻራ የመሬት መራቆትን በመከላከል ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እያስገኘ ነው” የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ኢብራሂም ኡስማን

7
አረንጓዴ ዐሻራ መርሐግብር በክልሉ የመሬት መራቆትን በመከላከል ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ እያስገኘ መሆኑን የሶማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ኢብራሂም ኡስማን ገልጸዋል።
’’ተስፋን እንትከል’’ በሚል መሪ ሀሳብ በክልሉ የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር እየተካሄደ ይገኛል።
ምክትል ርዕሰ መሥተዳድሩ በክልሉ ባለፉት ዓመታት በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር በተከናወኑ ተግባራት አመርቂ ውጤቶች እያስገኙ መሆኑን ገልጸዋል።
የአረንጓዴ ዐሻራ ችግኝ ተከላ መርሐግብር በክልሉ የመሬት መራቆትና የአፈር መሸርሸርን በመከላከል ምርታማነትን በማሳደግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው ብለዋል።
Previous articleየአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ ኢትዮጵያውያን ከተባበርን የማናሳካው እንደሌለ ማሳያ ነው።
Next articleየተተከሉትን ችግኞች እንደ ልጅ በመንከባከብ ለፍሬ ለማብቃት ቁርጠኛ መኾናቸውን የደብረ ታቦር ከተማ ነዋሪዎች ተናገሩ።