“የኅብረተሰብን ጤና መጠበቅ ለዘላቂ ሀገራዊ ብልጽግና መሠረት ነው” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመሥገን ጥሩነህ

11

 

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትን የሥራ እንቅስቃሴ ተመልክተዋል።

የኅብረተሰብ ጤና ድምር ውጤቱ በተሰማራበት ዘርፍ ሁሉ ውጤታማ ተግባር የሚከውን እና ለሀገሩ ሁለንተናዊ ብልፅግና የሚተጋ አምራች ኅብረተሰብ መገንባት ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያን ላለፉት 100 ዓመታት ያገለገለውን፣ ታሪካዊ ወረት እና ዘመናዊ አቅምን ያጣመረውን የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትን የሥራ እንቅስቃሴ ተመልክተዋል ነው ያሉት።

የኅብረተሰብን ጤና መጠበቅ ለዘላቂ ሀገራዊ ብልጽግና መሠረት ነውም ብለዋል። ተቋሙ በወረርሽኝ ልየታ፣ በበሽታ ክትትልና ምላሽ፣ በላብራቶሪ፣ በምርምር፣ በዲጂታላይዜሽን እና በጤና ስጋት ዝግጁነት የሀገሪቱን የጤና ሥርዓት በጥንካሬ እየደገፈ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

በክልሎች የድንገተኛ ኅብረተሰብ ጤና አደጋ መከላከያና መቆጣጠሪያ ማዕከላትን ማቋቋሙና የሪፈራል ላብራቶሪዎችን ማስፋፋቱ የሀገሪቱን የጤና ዝግጁነት አቅም እያጠናከረ ያለ ወሳኝ ተግባር ስለመኾኑም አንስተዋል።

በቀጣይም የአፍሪካ የኅብረተሰብ ጤና የልህቀት ማዕከል ለመሆን በከፍተኛ ትጋት እየሠራ ይገኛል። ከዚህ በተጨማሪም የዓለም የጤና ድርጅት የትብብር ማዕከል በመኾን ዓለም አቀፍ ሚናውን ለማጠናከር ብርቱ ጥረት እያደረገ የሚገኝ ተቋም ስለመኾኑ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አብራርተዋል።

“የትላንትን ታሪክ ጠብቆ፣ ዛሬን በዘመናዊነት ዋጅቶ፣ ወደ ነገ የሚገሰግስ እንደዚህ ያለ ተቋምን መደገፍና ማጠናከር ለነገ የማንለው ተግባር ነው” ብለዋል። ኢንስቲትዩቱ የሀገርን ብልፅግና ለማፋጠን ወሳኝ አቅም በመሆኑ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግም አረጋግጠዋል።

#አሚኮ #healthcare #Ethiopia

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleበሀረሪ ክልል የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት የዜጎችን ሕይወት በላቀ ደረጃ እየቀየረ ነው።
Next articleርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በመጠናቀቅ ላይ ያለውን የመገጭ ግድብ ጎበኙ።