
ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የመገጭ ግድብ ፕሮጄክትን ተዘዋውረው ተመልክተዋል። በጉብኝቱ ከርእሰ መሥተዳድሩ በተጨማሪ የአማራ ክልል ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ፣ የአማራ ክልል ምክትል ርእሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)፣ የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይን ጨምሮ ሌሎችም ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
የመገጭ ግድብ ፕሮጄክት ለአካባቢው አርሶ አደሮች ከፍተኛ የኾነ ለመስኖ ልማት አገልግሎት የሚሰጥ ነው። ከመስኖ ልማት ባለፈም የጎንደር ከተማ የንጹሕ መጠጥ ውኃ ችግርን በዘላቂነት እንደሚፈታ ተስፋ የተጣለበት ትልቅ ፕሮጄክት ነው።
ለዓመታት ሲጓተት የነበረው እና የሕዝብ ጥያቄ ኾኖ የኖረው መገጭ ግድብ አሁን ላይ በተሰጠው ልዩ ትኩረት በጥሩ አፈጻጸም ላይ ይገኛል። ፕሮጄክቱ 94 በመቶ አፈጻጸም ላይ መድረሱም ተገልጿል።
ከጥቂት ጊዜያት በኋላ ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት እንደሚኾን ይጠበቃል። አሁን ላይ 33 ሚሊዮን ሜትር ኪዩብ ውኃ ይዟል።
#ባሕር_ዳር #ነሐሴ_29_2018_ዓ_ም
ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
