የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ሠራተኞች እና የሥራ ኀላፊዎች “በአንድ ጀምበር” የችግኝ ተከላ የተከሏቸውን ችግኞች ለፍሬ እንደሚያበቁ ገለጹ።

7
የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ሠራተኞች እና የሥራ ኀላፊዎች “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ መልዕክት እየተካሄደ በሚገኘው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በተቋሙ ግቢ ችግኝ ተክለዋል።
አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ በግቢ ውስጥ የተለያዩ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸውን ችግኞች በመትከል የሌማት ትሩፋት ኢንሸቲቨን ተግባራዊ በማድረግ አትክልትና ፍራፍሬዎችን በስፋት እያመረተ ይገኛል።
በተቋሙ ግቢ ውስጥ የተተከሉት እንደ ፓፓያ፣ ማንጎ፣ ጎመን፣ ካሮት፣ ቀይ ስር፣ ፎሶሊያ፣ ካሮት፣ ቲማቲም፣ ሽንኩርት፣ ኩከምበር፣ ቆስጣ እና ሰላጣ ያሉ አትክልት እና ፍራፍሬዎች ሠራተኞችን ተጠቃሚ እያደረጉ ነው።
ከእነዚህ አትክል እና ፍሬፍሬ ችግኞች የሚገኘው ምርት ከመደበኛ ገበያ በግማሽ በቀነሰ ዋጋ ለሠራተኞቹ እየቀረበ እና ከፍተኛ ጥቅም እየሰጠ ይገኛል።
በተጨማሪም የተተከሉ ችግኞች ግቢውን ሳቢ እና ማራኪ በማድረግ ምቹ የሥራ ከባቢን ፈጥረዋል።
የተቋሙ ሠራተኞች እና የሥራ ኀላፊዎች ዛሬም “በአንድ ጀንበር” የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸውን ችግኞች በግቢ ውስጥ ሲተክሉም ለተከሏቸውን ችግኞች አስፈላጊውን እንክብካቤ በማድረግ ለፍሬ እንደሚያበቁ አረጋግጠዋል።
ዘጋቢ፦አድኖ ማርቆስ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous article“መሬት የመኖራችን ምስጢር ነች”
Next article“የአረንጓዴ ዐሻራ መርሀ ግብር የተራቆቱ አካባቢዎች እንዲለመልሙ እያደረገ ነው” የሲዳማ ክልል ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር በየነ በራሳ