ኢትዮጵያውያን በመተባበር ታሪክ መሥራት እንደምንችል ለዓለም ያሳየንበት መርሐ ግብር ኾኖ ቀጥሏል።

5
በሀገር አቀፍ ደረጃ “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ መልዕክት “በአንድ ጀምበር” የ800 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።
የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የቴክኒክ ኮሚቴ አስተባባሪ አደፍርስ ወርቁ (ዶ.ር) በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የሀገሪቱ ከግማሽ በላይ የሚኾነውን የተራቆተ መሬት ለመቀልበስ የተጀመረ ነው።
የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግር የኢትዮጵያን ሁለንተናዊ ዕድገት ለማረጋገጥ አስፈላጊ መኾኑ ታምኖበት ተግባራዊ የተደረገ ነው ብለዋል። በአየር ንብረት ለውጥ የማትበገር ሀገር ለመገንባት እና ሁለንተናዊ ብልጽግናን ለማረጋገጥ ሁሉም ዜጋ አሻራውን እንዲያሳርፍ ታስቦ ተግባራዊ የተደረገ ስለመኾኑም አብራርተዋል።
መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ዳር እስከ ዳር ተነቃንቆ በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብሩ እየተሳተፈ ነው ብለዋል። በእስከ አሁኑ አተገባበር የተራቆተው መሬት እያገገመ፣ የደረቁ ወንዞች እየተመለሱ፣ የአፈሩ ለምነት እየተሻሻለ፣ የደን ሽፋን እየጨመረ መጥቷልም ነው ያሉት።
በዚህም መርሐ ግብሩ “ኢትዮጵያውያን በመተባበር ታሪክ መሥራት እንደምንችል ለዓለም ያሳየንበት መርሐ ግብር ኾኖ ቀጥሏል” ነው ያሉት።
የዛሬውን መርሐ ግብር ለማሳካት እርብርብ እንዲደረግም ጥሪ አቅርበዋል።
ዘጋቢ:- አሰፋ ልጥገበው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleምሥራቅ ዕዝ ባደረገው የፀረ ሽምቅ ኦፕሬሽን 74 ፅንፈኞችን ደመሰሰ፡፡
Next articleለአካባቢ ጥበቃ እና ለምግብ ዋስትና ማረጋገጫ እየተተገበረ ያለ ሀገራዊ ግብ !