
ዕዙ በተሰማራባቸው ደቡብ ጎንደር፣ ሰሜን ጎጃም፣ ምዕራብ ጎጃም እና አዊ ብሔረሰብ አሥተዳደር ከሐምሌ 20 እስከ ሐምሌ 26/2018 ዓ.ም ባደረገው የተቀናጀ ስምሪት 49 ፅንፈኞች እርምጃ ተወስዶባቸዋል፤ 18ቱ ቆስለዋል። አንድ ሲማረክ፣ አራቱ ወደው ገብተዋል፣ ሁለቱ ደግሞ ተይዘዋል፡፡
በተደረገው ውጊያ ከተደመሰሱት የጽንፈኛው ቡድን አመራሮች ውስጥ፦
👉 ተመስገን አብርሀም፦ በነሱ አጠራር የተራራው ራስ ጉና ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ
👉 ጌታለም ምረት፦ ብርጌድ አዛዥ
👉 የሽዋስ ግዛቸው፦ ሻለቃ ኣዛዥ ይገኙበታል፡፡
በኦፕሬሽኑ 28 ኤ ኬ ኤም/ክላሽ፣ 21 የቃታ መሳሪያ፣ አንድ አር ፒ ጂ/ላውንቸው፣ ሰባት ቦንብተማርኳል። 500 የፈንጅ ፊውዝ ከነተቀጣጣይ ገመዶቹ እንዲሁም 180 ኪሎ ግራም ለፈንጅ ማቀጣጠያ የሚውል አልሙኒየም በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
በዚህ ስምሪት የምሥራቅ ዕዝ ኮር ከሽንዲ – አችጊ አደጋ ጉሽታ ድረስ፣ ከዝቋላ ተነስቶ – አረፋ – ቆላ ሸንጌ እንዲሁም ከሰከላ በአበስከን አቅጣጫ በመሰማራት ለጥፋት ተልዕኮ ራሱን ያዘጋጀውን ጽንፈኛ ቆርጦ በመምታት እና ቀጣናውን በመቆጣጠር ሕዝቡ የሰላም አየር እንዲተነፍስ አስችሏል፡፡ ከዚህ ጎን ለጎንም በፈረስ ቤት፣ በሰከላ፣ በሀሙሲት፣ በገነት አቦ እና ሌሎች አካባቢዎች የሚገኘው ሠራዊት ጽንፈኞችን የማጽዳት ግዳጁን እየተወጣ ይገኛል።
በሌላ አቅጣጫ የተሰማራው ሠራዊቱ ደግሞ ከቁንዝላ ተነስቶ አቦላ እና ካንቻዬ፣ ከግንብ ገረገራ አስተርዮ፣ ከዋሸራ ወደ ሐሙሲት መገንጠያ ላይ፣ በነጭ ውኃ ወይም ወይበይኝ፣ በአክሊ፣ በደብረ ወይፋት፣ በአንጎፌ እና በሌሎች ቀጣናዎች ከሞት ያመለጠውን ጽንፈኛ እየጠራረገ የተጣለበትን ተልዕኮ በብቃት እየፈፀመ ይገኛል።
በደቡብ ጎንደር ግዳጁን በመወጣት ላይ የሚገኘው የምሥራቅ ዕዝ አሀድ በተሰማራባቸው ከሳሊ ወደ አፋፍ፣ ከክምር ድንጋይ – ጥጥራ መገንጠያ፣ ከንፋስ መውጫ – አህያ ጥላ፣ ከሳሊ – አውራምባ፣ ከአርብ ገበያ – ሸጋው ማርዬ እና ሌሎች ቀጣናዎች የሚገኝን ፅንፈኛ በገባበት ገብቶ በመደምሰስ በአካባቢው ሰላም እያሰፈነ ይገኛል ፡፡
ምሥራቅ ዕዝ ከሐምሌ 20/2018 ዓ.ም ወዲህ ባደረጋቸው የሰባት ቀናት ተከታታይ ስምሪቶ፣ ዘራፊውን ቡድን ከቦ በመደምሰስ፣ በየሸጡ የተወተፈውን በማጽዳት ያደረገው እልህ አስጨራሽ ግዳጅ የየአካባቢው ሕዝብ እፎይ እንዲል አስችሏል፡፡
በየግዳጅ ቀጣናው የክልሉ የጸጥታ ኃይል ከሠራዊቱ ጎን ተሰልፎ አኩሪ ግዳጅ ፈጽሟል፡፡ በዚህም 4 የብሬን ቃታ፣ 2 የብሬን ቅያሬ አፈሙዝ፣ 2 የስናይፐር መነፅር፣ 2 የስናይፐር ቃታ፣ 22 የዙ-23 መሳሪያ ጥይት ከነ ሸንሸሉ፣ 8 የወገብ ትጥቅ፣ 1 ጀኔሬተር፣ 2 ከሕዝብ የተዘረፉ ከባድ ተሸከርካሪዎችን እና ሌሎች ቡድኑ ሲጠቀምባቸው የነበሩ የሎጀስቲክስ ቁሳቁሶች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡ ጽንፈኛው ከሕዝብ በመዝረፍ ለእርድ ያዘጋጃቸው 6 ከብቶች እና 5 ፍየሎችም ተይዘዋል።
የፀረ ሽምቅ ስምሪቱ በፈጠረው ምቹ ሁኔታ የየአካባቢው መሥተዳድር እግር በግር እየገባ ሕዝብን በማወያየት እና የጠላትን ሴልና ንብረት እየለየ በሕግ ስር እያዋለ ይገኛል።
ምሥራቅ ዕዝ የኢትዮጵያን ማደግ የማይሹ ያሰማሯቸውን የጥፋት መልዕክተኞችን ዱካ እየተከታተለ ከየተደበቁበት ጎሬ እየለቀመ የሀገራችንን ሰላም ያስቀጥላል፡፡ በባዕዶች ፈረስ የተፈናጠጡትን የኛን ተላላኪዎች ከየተወሸቁበት እያደነ ሕግ ማስከበሩን ይቀጥላል፡፡
ዘገባው የምስራቅ ዕዝ ነው።
#አሚኮ #defencenews #ethiopia
#ባሕርዳር ሐምሌ 27/2018ዓ.ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
