«ዛሬ የማሳርፈው አሻራ የልጆቼን የነገ ሕይወት ብሩህ ያደርጋል» የኮምቦልቻ ከተማ ነዋሪ

7

 

የኮምቦልቻ ከተማ ነዋሪው ሼህ ሙሃመድ ስይድ ፀሐይ ሳትወጣ በማለዳው ቀድመው ሦሥት ሕጻናት ልጆቻቸውን ይዘው ወደ ተዘጋጀው የችግኝ መትከያ “መንጠራ” ተፋሰስ አምርተዋል።

በቦታው ለነበሩት በርካታ የኅብረተሰብ ክፍሎችም ልዩ ብርታት እና የደስታ ምንጭም ኾነዋል።

«ዛሬ የምንተክላት እያንዳንዷ ችግኝ ለአፈሩ ጥበቃ ብቻ ሳይኾን ለእነዚህ ልጆቼ የምተወው ትልቅ ሀብት እና የነገ ተስፋ ነው ብለዋል።

ሀገርን ለአዲሱ ትውልድ አረንጓዴ አድርጎ ማስረከብ የሁላችንም አባታዊ እና ሀገራዊ ግዴታ ነው ሲሉም ተናግረዋል::

ሼህ ሙሃመድ ስይድ መላ ቤተሰቡ በቤታቸው አካባቢ ችግኝ ተክለው እንደሚንከባከቡ ገልጸው ከማኅበረሰቡ ጋር በጋራ መትከላቸው ደግሞ አብሮነትን እና በጋራ መቆምን እንደሚያጠናክር ነው የገለጹት::

በቀጣይም የተተከሉትን ችግኞች በመንከባከብ የድርሻቸውን እንደሚወጡም ቃል ገብተዋል::

#AMECO #greenlegacy #Ethiopia

#ደሴ #ሐምሌ_27_2018_ዓ_ም

ዘጋቢ፦ደጀን አምባቸው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article“አረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የሰው ልጅን ከተፈጥሮ ጋር እያቆራኘ ነው”
Next articleምሥራቅ ዕዝ ባደረገው የፀረ ሽምቅ ኦፕሬሽን 74 ፅንፈኞችን ደመሰሰ፡፡