በአንድ ጀምበር እስከ አሁን ከ578 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን መተከላቸውን የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ ገልጸዋል።

5
የ2018 ዓ.ም በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ ዛሬ ዕለት በመላ ሀገሪቱ እየተካሄደ ነው፡፡
የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ (ዶ.ር) የዘንድሮው የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር በተሳካ ሁኔታ እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
መላው ኢትዮጵያዊ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ጥሪ በመቀበል ሕዝቡ ከማለዳው 12 ሰዓት ጀምሮ በነቂስ ወጥቶ ችግኝ እየተከለ መሆኑን ገልጸዋል።
በአንድ ጀምበር እስከ አሁን ከ578 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን መተከላቸውን ገልፀው፤ ይህም ለመትከል ከተያዘው እቅድ 72 ከመቶ መሆኑን ጠቁመዋል።
በቀሪ ሰዓታትም የተቀረውን ቁጥር ማሳካት የሚያስችል ርብርብ እየተደረገ መሆኑን በመግለጫቸው ገልጸዋል።
Previous article“የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የአርሶ አደሮችን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ ነው”
Next article“አረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የሰው ልጅን ከተፈጥሮ ጋር እያቆራኘ ነው”