“የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የአርሶ አደሮችን ተጠቃሚነት እያረጋገጠ ነው”

3
የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የ800 ሚሊዮን የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብርን በደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ በጨለቃ ክላስተር በመገኘት አሻራቸውን አስቀምጠዋል።
ከርእሰ መሥተዳድሩ በተጨማሪ የኢትዮ ጅቡቲ ባቡር መስመር ሥራ አሥኪያጅ ኢንጅነር ታከለ ኡማ እና የክልል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎችም ተገኝተዋል።
የደቡብ ወሎ ዞን አሥተዳዳሪ አሊ መኮንን በዞኑ በዘንድሮው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር 230 ሚሊዮን ችግኝ በ54 ሺህ 600 ሄክታር መሬት ላይ ለመትከል እየተሠራ ነው ብለዋል።
በዞኑ ባለፉት ሰባት ዓመታት የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ችግኝ ተተክለዋል ነው ያሉት። በዚህም የዞኑን የደን ሽፋን ከ9 በመቶ ወደ 15 ነጥብ 7 በመቶ ማሳደግ ተችሏል ብለዋል።
በበጋ ወራት በ447 ሄክታር መሬት ላይ 326 ሺህ የሙዝ፤ የፓፓያ እና የማንጎ ችግኝ መተከሉንም አንስተዋል።
በዞኑ 38 ሄክታር መሬትን ከጫት በማጽዳት የአትክልት እና ፍራፍሬ ልማት ተጠቃሚ እንዲኾኑ ማድረግ ተችሏል ነው ያሉት።
የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኀላፊ ደረጀ ማንደፍሮ ባለፉት ዓመታት የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር 10 ነጥብ 6 ቢሊዮን ችግኞች መተከላቸውን ገልጸዋል።
ከ1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በላይ በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር መሸፈኑንም ገልጸዋል።
በክልሉ በአንድ ጀምበር 327 ሚሊዮን ችግኞች እንደሚተከሉም ጠቅሰዋል።
በደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ በጨለቃ ክላስተር በ213 ሄክታር መሬት የማንጎ ክላሥተር አርሶ አደሮችን በአንድ በማደራጀት ችግኞች እየለሙ መኾኑንም አንስተዋል።
ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleበአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የተፈጥሮ ሚዛንን በመጠበቅ የዜጎችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ መቻሉን የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር እንዳሻው ጣሰው (ዶ.ር) ተናገሩ።
Next articleበአንድ ጀምበር እስከ አሁን ከ578 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን መተከላቸውን የግብርና ሚኒስትር አዲሱ አረጋ ገልጸዋል።