
ኢትዮጵያውያን በዛሬው ዕለት በአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል ሂደቱን በስኬት ለማጠናቀቅ ከማለዳው አንስቶ እየተሳተፉ ይገኛሉ።
በዚህም ርዕሰ መስተዳድሩ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በጉራጌ ዞን በቀቤና ልዩ ወረዳ ፈረጀቴ ቀበሌ በሬቡ ተፋሰስ በመገኘት አረንጓዴ ዐሻራቸውን አኑረዋል።
ርዕሰ መስተዳደሩ እንዳሉት በአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር የተፈጥሮ ሚዛንን በመጠበቅ የዜጎችን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ተችሏል።
የሚተከሉ የፍራፍሬና ሌሎች ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ተፈጥሮን በመጠበቅ የምግብ ዋስትናን የማረጋገጥ ስኬት እያስመዘገቡ መሆኑንም ገልጸዋል።
#AMECO #greenlegacy #Ethiopia
