
በሀገር አቀፍ ደረጃ “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ መልዕክት “በአንድ ጀምበር” የ800 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።
በመርሐ ግብሩ መልዕክት ያስተላለፉት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እጅግ ስኬታማ በኾነ መንገድ እየተከናወነ እንደኾነም አስረድተዋል።
መርሐ ግብሩ የዘመቻ ሥራ ሳይኾን “ከተፈጥሮ ጋር የምንስማማበት እና ዘላቂ ልማትን የምናረጋግጥበት ዓይነተኛ መሣሪያ ነው” ብለዋል።
በመርሐ ግብሩ አጠቃላይ የኢትዮጵያን ሕዝብ በማሳተፍ በሰባት ዓመታት ውስጥ ከ48 ቢሊዮን በላይ ችግኞችን መትከል እንደተቻለም ጠቁመዋል።
በዛሬው መርሐ ግብርም መላው ኢትዮጵያውያን በነቂስ ወጥተው አሻራቸውን እንዲያሳርፉም መልዕክት አስተላልፈዋል።
ዘጋቢ:- አሰፋ ልጥገበው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
