“ቀጣናውን የአትክልት እና ፍራፍሬ ኮሪደር ለማድረግ እየተሠራ ነው”

3

 

በሰሜን ወሎ ዞን የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በመርሳ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል።

የዞኑ ግብርና መምሪያ ኀላፊ ተገኝ አባተ በዞኑ ከ167 ሚሊዮን በላይ ችግኝ ለተከላ የተዘጋጀ ሲኾን በአንድ ጀምበር 28 ነጥብ 8 ሚሊዮን ችግኝ ይተከላል ብለዋል።

የሰሜን ወሎ ዞን ዋና አሥተዳዳሪ አራጌ ይመር ዞኑን የፍራፍሬ ኮሪደር ለማድረግ ታላሚ ያደረገ የችግኝ ተከላ እየተካሄደ መኾኑን ለአሚኮ ገልጸዋል።

በደጋማው ክፍል የአኘል፤ በቆላማው ደግሞ ሙዝ፣ ማንጎ፣ አቦካዶ እና ፓፓያን የመሳሰሉ ችግኞች በክረምት አረንጓዴ አሻራ እና በበጋ እየተተከለ ነውም ብለዋል።

ችግኞችን መትከል ብቻውን ግብ አለመኾኑን ያነሱት ዋና አሥተዳዳሪው ለተተከሉ ችግኞች አስፈላጊውን እንክብካቤ ማድረግ ከማኅበረሰቡ ይጠበቃል ነው ያሉት።

#AMECO #greenlegacy #Ethiopia

#ደሴ #ሐምሌ_27_2018_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleበአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የታየውን አንድነት በሰላም ተግባርም መድገም ይገባዋል።
Next article“የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ከተፈጥሮ ጋር የምንስማማበት ዓይነተኛ መሣሪያ ነው” አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ