በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የታየውን አንድነት በሰላም ተግባርም መድገም ይገባዋል።

2

 

በጎንደር ከተማ አሥተዳደር የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የከተማዋ ነዋሪዎች በተገኙበት እየተከናወነ ይገኛል።

በመርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የሰላም ሚኒስቴር የብቃት እና የሰው ሀብት አሥተዳደር ሥራ አሥፈጻሚ ኮሪ አብደላ በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ላይ በጎንደር ተገኝተው አሻራቸውን አስቀምጠዋል። የሰላም ንቅናቄ መርሐ ግብር ይዘው መምጣታቸዎን ገልጸው ችግኝ በመትከል አንድነታችንን አሳይተናል ብለዋል።

በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ላይ የታየው አንድነት በሰላም እና መግባባት መፍጠር ላይም መድገም እንደሚገባ ነው የገለጹት።

በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ላይ የተሳተፉ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች በተደጋጋሚ ችግኝ መትከላቸውን ገልጸዋል። ላለፉት ዓመታት የተተከሉ ችግኞች በማኅበረሰቡ ሕይወት ላይ ለውጥ እያመጡ መኾኑን ለአሚኮ ተናግረዋል።

በጎንደር ከተማ የአትክልት እና ፍራፍሬ ምርቶች ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት ይታያል ያሉት አስተያየት ሰጭዎቹ የተተከሉ የአትክልት እና ፍራፍሬ ምርቶች እንዲጸድቁ በማድረግ የገበያ መረጋጋት እንዲፈጠር መሥራት ይገባል ነው ያሉት።

የኢትዮጵያውያን ትብብር እና አንድነት በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ታይቷል ያሉት ነዋሪዎቹ ሰላም ላይም መምጣት እና በሀገር ግንባታ ላይ አንድነታችንን ማሳየት ይገባናል ብለዋል።

#AMECO #greenlegacy #Ethiopia

#ጎንደር #ሐምሌ_27_2018_ዓ_ም

ዘጋቢ፦ ደስታ ካሣ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article“አረንጓዴ ዐሻራ የአየር ንብረት ለውጥን ከመከላከል ባለፈ ለምግብ ዋስትናም ትልቅ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው” ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ.ር)
Next article“ቀጣናውን የአትክልት እና ፍራፍሬ ኮሪደር ለማድረግ እየተሠራ ነው”