
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ርዕሰ መስተዳድር ነጋሽ ዋጌሾ (ዶ.ር) በቤንች ሸኮ ዞን ደቡብ ቤንች ወረዳ በአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አሻራቸውን አኑረዋል፡፡
ርዕሰ መስተዳድሩ የአረንጓዴ ዐሻራ ለአየር ንብረት ለውጥ መቋቋም፣ የአፈር ጥበቃና ለምነት ማሻሻል እንዲሁም ለምግብ ዋስትና መረጋገጥ ጉልህ አስተዋጽኦ እያበረከተ ነው ብለዋል።
በክልሉ በአንድ ጀምበር ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር 25 ሚሊየን ችግኞች እንደሚተከሉ ተናግረዋል። ችግኞቹ ለቀጣይ ትውልድ ዘላቂ ጥቅም እንዲያመጡ በአግባቡ መንከባከብና መጠበቅ ይገባል ነው ያሉት፡፡
አረንጓዴ ዐሻራ የአየር ንብረት ለውጥን ከመከላከል ባለፈ በምግብ ራስን ለመቻል ለሚደረገው ጥረት ትልቅ ሚና እየተጫወተ እንደሚገኝም አመልክተዋል፡፡
#AMECO #greenlegacy #Ethiopia
#ሐምሌ_27_2018_ዓ_ም
