ችግኝ በመትከል ሕልውናን የመታደግ ኀላፊነት በደብረ ብርሃን !

3
🌿
በደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ግብርና መምሪያ አሥተባባሪነት የ”ተስፋን እንትከል” የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የከተማዋን ማኅበረሰብ ባሳተፈ ንቅናቄ እየተከናወነ ይገኛል።
የከተማ አሥተዳደሩ ግብርና መምሪያ በዘንድሮው የክረምት ወቅት 9 ነጥብ 1 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል አቅዶ ወደ ሥራ ገብቷል።
በዛሬው ዕለት ብቻ 550 ሺህ ችግኞችን በአንድ ጀምበር ለመትከል የተያዘው ግብ በከፍተኛ ሕዝባዊ ተሳትፎ እየተከናወነ ነው።
ይህ ጥረት የከተማዋን እና የአካባቢዋን የተፈጥሮ ሀብት ለመንከባከብ፣ የደን ሽፋን ለማሳደግ እና የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የሚደረገውን ሀገራዊ ጥረት በእጅጉ የሚያጠናክር ነው።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleየየክልሎች የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ እቅድ ምን ይመስላል?