በሶማሌ ክልል በረሃማነትን የሚገዳደረው ታሪካዊው የአንድ ጀምበር አረንጓዴ አሻራ በደማቁ እየተካሄደ ነው።

5

 

በሶማሌ ክልል ከማለዳው 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ታሪካዊው “የአንድ ጀምበር” የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በይፋ ተጀምሮ በከፍተኛ የህዝብ ተሳትፎ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

በክልሉ በሚገኙ 91 የተመረጡ የመትከያ ቦታዎች በነቂስ ወጥቶ እየተከናወነ ያለው ይህ ደማቅ መርሃ ግብር፣ በዋናነት የክልሉን በረሃማነት በሚያስቀሩና ለድርቅ ያለውን ተጋላጭነት በሚቀንሱ ለአየር ንብረት ተስማሚ በሆኑ ችግኞች ላይ ልዩ ትኩረት አድርጓል።

ባለፉት ሰባት ዓመታት በተተገበረው ስኬታማ የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር፣ በክልሉ የአየር ንብረት ለውጥ ያመጣውን ተጽዕኖና ተጋላጭነት ትርጉም ባለው መልኩ መቀነስ ተችሏል።

የክልሉ ሕዝብም ይህንን ከዚህ ቀደም የተመዘገበውን አዎንታዊ ውጤት በሚገባ በመረዳት፣ በዛሬው ዕለት 800 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ጀምበር ለመትከል የተያዘውን ሀገራዊ ግብ ለማሳካት በከፍተኛ መነሳሳት ዐሻራውን እያሳረፈ ይገኛል።

ማህበረሰቡ በተፈጥሮ ላይ ያለውን ጥልቅ ፍቅር እያሳየበት የሚገኘው እና ዛሬ ማለዳ የተጀመረው ይህ ሀገር አቀፍ የችግኝ ተከላ ዘመቻ እስከ ምሽት ድረስ በከፍተኛ ድምቀት ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ታውቋል፡፡ ዘገባው የኢቢሲ ነው።

#AMECO #greenlegacy #Ethiopia

Previous article“አካል ጉዳተኛነት ተስፋችንን ከመትከል አያግደንም” አካል ጉዳተኞች
Next articleየየክልሎች የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ እቅድ ምን ይመስላል?