“አካል ጉዳተኛነት ተስፋችንን ከመትከል አያግደንም” አካል ጉዳተኞች

4

 

አካል ጉዳተኛነት ሀገራዊ ጥሪን በመቀበል የነገን ተስፋ ከመትከል እንደማያግዳቸው በባሌ ዞንና ሮቤ ከተማ አስተዳደር በአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ የተሳተፉ አካል ጉዳተኞች ገልጸዋል።

በዛሬው ዕለት በመላው የሀገሪቷ ክፍሎች በአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሃ ግብር እየተካሄደ ይገኛል።

በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞንና በሮቤ ከተማ አስተዳደር የ”አንድ ጀምበር” የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ከማለዳው ጀምሮ ሕዝባዊ ተሳትፎ እየተካሄደ ነው።

“የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ለትውልድ ታስቦ የሚከናወን በመሆኑ፣ አካል ጉዳተኝነት ሳያግደን የነገ ተስፋና ስንቅ የሆነውን ችግኝ ከመትከል አላገደንም” ብለዋል በችግኝ ተከላው የተሳተፉ አካል ጉዳተኞች።

መርሃ ግብሩ ሁሉንም እኩል ተጠቃሚ የሚያደርግ መሆኑን በመረዳት፣ ማንኛውም የኅብረተሰብ ክፍል በንቃት እንዲሳተፍም ጥሪ አቅርበዋል።

በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ.ር) የቀረበውን ሀገራዊ ጥሪ በመቀበል አካል ጉዳተኝነት ሳይገድባቸው በችግኝ ተከላ በመሳተፍ ላይ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

የሮቤ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ጀማል አባገሮ በበኩላቸው፤ በአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ላይ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ከማለዳው ጀምሮ በንቃት እየተሳተፉ መሆኑን ገልጸዋል።

በተለይም አካል ጉዳተኞች ያለ ምንም እንቅፋት በመርሃ ግብሩ ላይ በቁርጠኝነት መሳተፋቸው ለሌሎች ነዋሪዎች ትልቅ መነሳሳትን እንደፈጠረ ተናግረዋል።
#AMECO #greenlegacy #Ethiopia

#ሐምሌ_27_2018_ዓ_ም

Previous articleየጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) መልዕክት፦
Next articleበሶማሌ ክልል በረሃማነትን የሚገዳደረው ታሪካዊው የአንድ ጀምበር አረንጓዴ አሻራ በደማቁ እየተካሄደ ነው።