የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) መልዕክት፦

4

 

አረንጓዴ ዐሻራ የመበልጸግ ጉዞ አንዱ ሰበዝ!

• ሥልጣኔ የነጠላ ተግባር ውጤት አይደለም፤ የአንድ ዘርፍ እድገትም ብቻውን አያሰለጥንም
• የአረንጓዴ ዐሻራ ሥራችን የአንድ ሰሞን ዘመቻ አይደለም፤ የአጭር ጊዜ ግብን ታሳቢ ያደረገ ቁንጽል እርምጃ አይደለም!

• አረንጓዴ ዐሻራ፦ የትልቁ ዓላማችን አንድ ሰበዝ ነው። እንደ ሀገር የመበልጸግና የሁለንተናዊ እድገት ጉዟችን አካል ነው።

አረንጓዴ ዐሻራ፤ ሌላኛው የሥልጣኔ መሰረት!

• ሥልጣኔ ባዶ አየር ላይ አይገነባም፤ ጠንካራ መሰረት ይፈልጋል።
• መሰረት ሳይጸና የሚገነባ ነገር በቀላሉ ፈራሽ ነው፣ አይዘልቅም።

• ዘመናትን የሚሻገር ስልጣኔ በመሰረቱ ጥልቀት ይታወቃል። የዛሬ አረንጓዴ ዐሻራ ከብዙ የሥልጣኔ መሰረቶች አንዱ ነው!

• ልክ እንደ ኢነርጂ ልማት፣ የኢንደስትሪ ማስፋፋት፣ እንደ ክህሎት ግንባታ ወዘተ የሚታይ ነው።

ስነ-ምኅዳራዊ ዘላቂነት ለጠንካራ ሥልጣኔ

• ሀገረ-መንግሥታዊ ግንባታን ለማጠናከር ተቋማትን እንደምንገነባው፤ አብሮነታችንን ለማጠናከር ሀገራዊ እርቅና ምክክር ላይ እንደምንረባረበው፤ የኢኮኖሚያችን መዋቅራዊ ሽግግር ለማምጣት ኢንዱስትሪና ዲጅታል ዘርፎች ላይ እንደምናተኩረው፤ የሁሉም ዐሻራ ያረፈባት ሀገርና ባለቤትነትን ለማጽናት አስተዳደራዊ ልህቀት ላይ እንደምንሰራው፤ ስነ-ምኅዳራዊ ዘላቂነትን ለማምጣት አረንጓዴ ዐሻራ ላይ መስራት ይገባል።

• ምክንያቱም አብሮነት ካልተጠበቀ፣ የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር ካልተካሄደ ሥልጣኔ እንደማይሳካው፤

• ሀገረ-መንግሥት ግንባታ ካልጠነከረ ሥልጣኔ እንደማይዘልቀው ሁሉ፤ ስነ-ምኅዳራዊ ዘላቂነት ካልመጣ ሥልጣኔ አይዘልቅም።

• የአንዱ መጉደል ሥልጣኔን ምሉዕ አያደርግም!
ተስፋን በመትከል መሰረታችንን እናጽና!

Previous article“የአረንጓዴ አሻራ ምንጮች እንዲጎለብቱ እና ምርት እና ምርታማነት እንዲጨምር አድርጓል” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ
Next article“አካል ጉዳተኛነት ተስፋችንን ከመትከል አያግደንም” አካል ጉዳተኞች