የምግብ ዋስትና ስጋትን ሰው ሰራሽ አስተውሎት ይታደግው ይኾን?

18
ባሕር ዳር፡ ነሐሴ 27/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በአየር ንብረት ለውጥ፣ በሕዝብ ቁጥር እድገት እና በጂኦ ፖለቲካዊ አለመረጋጋት ምክንያት በአኹኑ ወቅት የዓለም የምግብ ሥርዓት አደጋ ውስጥ መውደቁን የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም መረጃ ያሳያል።
አርሶ አደሮች በቆየው ልማዳዊ አሠራር ስለሚመሩ ከድርቅ፣ ከዝናብ መዛባት እና ከአዳዲስ ሰብል ተባዮች ጋር ለመታገል ተገደዋል። በተለይም የአየር ንብረት መዛባት በሰብል ምርት መጠን ላይ ቀጥተኛ እና ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ይገኛል።
የመንግሥታት የአየር ንብረት ለውጥ ፓነል (IPCC) መረጃ እንደሚያሳየው የበካይ ጋዞች ሥርጭት አኹን ባለው ኹኔታ የሚቀጥል ከኾነ በሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት የበቆሎ ምርት በዓለም አቀፍ ደረጃ እስከ 24 በመቶ ሊቀንስ ይችላል።
ከዚህም ባሻገር የሙቀት መጨመር አዳዲስ በሽታዎችን እና ተባዮችን በማስፋፋት፣ አነስተኛ አርሶ አደሮችን ለከፍተኛ ሥጋትና ጉዳት ዳርጓቸዋል።
✍️ችግሮችን ለመመከት የሰራሽ አስተውሎት ሚናስ?
#ቴክኖሎጂው የበሽታ እና የተባይ ምልክቶችን በሰው ዓይን ከመታየታቸው ከሳምንታት በፊት በቅድመ ምርመራ የመለየት አቅም አለው።
በተጨማሪም በአንድ አካባቢ የታየን የሰብል ሥጋት ለሌላው በማሳወቅ እንደ ማዕከላዊ አእምሮ ያገለግላል።
ፈርማታ (Fermata) የተባለው አግሮ-ቴክኖሎጂ ኩባንያ እንደገለጸው በሰው ሰራሽ አስተውሎት የተደገፈው የተባይ መለያ ዘዴ ከተለመደው የሰው ኃይል ፍተሻ ከሦስት እስከ አምስት ሳምንታት ያህል ፈጣን ኾኖ ተኝቷል።
#አርሶ አደሮችን በማብቃት፦ ቴክኖሎጂው አርሶ አደሮች መቼ ማጠጣት፣ ማዳበሪያ ማድረግ ወይም ጠቃሚ ነፍሳትን መልቀቅ እንዳለባቸው በመጠቆም ብክነትን እንዲቀንስ በማድረግ ትል ዕድል አምጥቷል።
#በአጠቃላይ የሰው ሰራሽ አስተውሎት እና የግብርና ትስስር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ትልቅ ተስፋ ኾኗል።
የአሚኮ ዲጅታል ቤተሰብ ይኹኑ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!
Previous articleሞት እና እገታ ያብቃ በአዲሱ ዓመት
Next articleመሬትን ከይዞታ ማረጋገጫ ወደ ፋይናንስ አቅም ያዘመነው አዲሱ አሠራር።