
የኢትዮ ቴሌኮም ማዕከላዊ ሰሜን ሪጅን በደብረ ብርሃን ኢንዱስትሪ ፓርክ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብርን አከናውኗል።
ኢትዮ ቴሌኮም በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ሀገራዊ ኀላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ የገለጹት የሪጅኑ ኦፕሬሽን ዳይሬክተር አንተነህ ፋንታሁን ናቸው። ተቋማቸው ለ8ኛ ዙር “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ መልዕክት ዘመቻ ላይ በንቃት እየተሳተፈ መኾኑን ተናግረዋል።
በበረሃማነት መስፋፋት እየተፈተን ባለንበት በአሁኑ ወቅት የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ምድራችንን ለመታደግ እና ለመጠበቅ ፍቱን መፍትሔ እንደኾነ ገልጸዋል።
“ችግኝ መትከል ሕልውናን መታደግ እና መጠበቅ እንደኾነም” ተናግረዋል።
በተከላው ላይ የተሳተፉት የሪጅኑ ሠራተኞች ዋና ሳጅን ታምሬ ማሞ እና ተስፋ ፍስሐ ከመትከል ባሻገር የተተከሉት ችግኞች እንዲጸድቁ አስፈላጊውን ክትትል ለማድረግ ቁርጠኛ መኾናቸውን አረጋግጠዋል።
#AMECO #greenlegacy #Ethiopia
#ደብረ_ብርሃን #ሐምሌ_27_2018_ዓ_ም
ዘጋቢ፦ ሥነጊዮርጊስ ከበደ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
