ከመትከል ባለፈ ለችግኞች እንክብካቤ እየተደረገ ነው።

1
የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን “የአንድ ጀምበር” የችግኝ ተከላ መርሐግብርን አካሂደዋል።
በኢትዮጵያ “የአንድ ጀምበር” 800 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል መርሐግብር ላይ ተሳታፊ የኾነው የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን “በአንድ ጀምበር” 20ሺህ ችግኞችን በቦሌ ክፍለ ከተማ ገርጂ ማርያም ቤተክርስቲያን አካባቢ የመትከል መርሐ ግብር አካሂዷል።
የገቢዎች ሚኒስትር ዴኤታ ዳዊት ውብሸት ገቢዎች ሚኒስቴር ባለፉት ዓመታት እንደ ሀገር የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብርን በመሳተፍ እና ችግኞችን በመትከል ብሎም በመንከባከብ ሰፊ ሥራዎች እየሠራ መኾኑን ገልጸዋል።
የጉምሩክ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር አዘዘው ጫኔ በበኩላቸው ኮሚሽኑ ከዚህ በፊት የተተከሉ ችግኞችን ሠራተኞች በመቅጠር የመንከባከብ ሥራዎች ተሠርተዋል ነው ያሉት። አሁን የተተከሉትን ጨምሮ የመንከባከቡ ተግባርም ተጠናክሮ ይቀጥላልም ብለዋል።
“ተስፋን እንትከል” የ800 ሚሊዮን የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ላይ የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ሠራተኞች ተሳታፊ ኾነዋል።
ዘጋቢ፦ ሰሎሞን አሰፌ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous article“የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በርካታ የዲፕሎማሲ ድሎች እንዲገኙ አስችሏል” አቶ አደም ፋራህ
Next article“ችግኝ መትከል ሕልውናን መታደግ እና መጠበቅ ነው”