“የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በርካታ የዲፕሎማሲ ድሎች እንዲገኙ አስችሏል” አቶ አደም ፋራህ

9
በሀገር አቀፍ ደረጃ “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ መልዕክት በአንድ ጀምበር የ800 ሚሊዮን የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።
በመርሐ ግብሩ መልዕክት ያስተላለፉት በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ኀላፊ እና የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዝዳንት አደም ፋራህ “በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በርካታ የዲፕሎማሲ ድሎች እንዲገኙ አስችሏል” ብለዋል።
የኢትዮጵያን ገጽታ በመገንባት ተጽዕኖ ፈጣሪነትን ለማሳደግ እንዳስቻለም ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ በንግግር ሳይኾን በተግባር የአየር ንብረት ለውጥ መፍትሄ እንዲያገኝ በማድረግ ለዓለም እያስመሰከረች መኾኑንም አንስተዋል።
የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ እና ለሀገራችን ሁለንተናዊ ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያበረከተ እንደሚገኝም ገልጸዋል።
የዜጎች ሀገራዊ አንድነት እንዲጠናከር እና ማኅበራዊ ካፒታል እንዲያድግ አስችሏልም ነው ያሉት። ዜጎች ለሀገራዊ ግንባታ እንዲተባበሩ እና በአንድነት እንዲሰለፉም አስተዋጽኦ አድርጓል ብለዋል።
ዘጋቢ:- አሰፋ ልጥገበው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous article“የአረንጓዴ አሻራ ልማት ከተጀመረ አንስቶ የምግብ ሉዓላዊነታችንን እያረጋገጥን ነው” የገንዳውኃ ከተማ ነዋሪዎች
Next articleከመትከል ባለፈ ለችግኞች እንክብካቤ እየተደረገ ነው።