
“የአንድ ጀምበር” የአረንጓዴ አሻራ መርሐግብር በምዕራብ ጎንደር ዞን እየተካሄደ ነው።
በምዕራብ ጎንደር ዞን “በጋራ ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ መልዕክት “የአንድ ጀምበር” የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።
የአረንጓዴ አሻራ ልማት ከተጀመረ አንስቶ የምግብ ሉዓላዊነታችንን እያረጋገጥን ነው ሲሉ የገንዳውኃ ከተማ ነዋሪዎች ተናግረዋል።
ዛሬ የሚተክሉት ችግኞች ለነገ ለልጆቻቸው ውርስ እንደኾነ ነዋሪዎች ገልጸዋል። የሚተከሉትን ችግኞች እንደሚንከባከቡ እና እንደሚኮተኩቷቸውም ተናግረዋል።
ዘጋቢ፦ ኤሊያስ ጋሻው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
