‘’ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም ኀላፊነቷን እየተወጣች ነው” ጫልቱ ሳኒ

2
የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር የ800 ሚሊዮን የአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ላይ ተግባራዊ ተሳትፎ እያደረገ ነው፡፡
የሚኒስቴሩ ሠራተኞች እና የሥራ ኀላፊዎች የችግኝ ተከላውን ያካሄዱት በአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ ሦሥት ነው፡፡
የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስትሯ ጫልቱ ሳኒ ኢትዮጵያ የዓለም አቀፍ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የራሷን ኀላፊነት በተግባር እየተወጣች ነው ብለዋል።
የተተከሉት ችግኞች አድገው ጥቅም ላይ እስከሚውሉ ከሚኒስቴሩ ተጠሪ ተቋማት እና ከሴፍትኔት አባላት ጋር ክትትል እና እንክብካቤ እንደሚደረግም ገልጸዋል።
የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ዲኤታ ፋንታ ደጀን ችግኝ መትከል ለሀገር ውለታ መዋል ነው፤ ይህ በጎ ባሕል ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።
ዘጋቢ፦ አየለ መስፍን
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleስምንት ዓመታት፤ ቀጣይነት ባለው ተግባር!
Next article“የአረንጓዴ አሻራ ልማት ከተጀመረ አንስቶ የምግብ ሉዓላዊነታችንን እያረጋገጥን ነው” የገንዳውኃ ከተማ ነዋሪዎች