
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) መልእክት ፦
የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ-ግብር በሕዝባዊ ቁርጠኝነት እና ኢትዮጵያውያን በጋራ በመሆን አረንጓዴ እና ዘላቂነት ያለው ነገን መገንባት ይችላሉ በሚለው የጋራ እሳቤ እየተመራ ይበልጥ እየጠነከረ ቀጥሏል።
ዛሬ ኢትዮጵያውያን ለቀጣዩ ትውልድ የሚተርፍ ዘላቂ ዐሻራ ለማሳረፍ በጋራ የሚሰባሰቡበት ዓመታዊው የአንድ ጀምበር ሀገር አቀፍ የችግኝ ተከላ መርሃ-ግብራችን ነው።
ከቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው ጋር እንዲሁም ከኮፕ32 ብሔራዊ ኮሚቴ ጋር በመሆን የራሳችንን ዐሻራ በማሳረፍ ለዚህ የጋራ ጉዞ የበኩላችንን አስተዋፅኦ አበርክተናል።
የተቀመጠውን 800 ሚሊዮን ችግኝ የመትከል ታላቅ ግብ ለማሳካት በጋራ እየሰራን በመሆኑ፣ ኢትዮጵያውያን ቀኑን ሙሉ ጥረታችሁ እንዲቀጥል ጥሪዬን አቀርባለሁ።
