“የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የምናልመውን ሁሉ ዕውን ያደረግንበት ነው” ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ

5
በሀገር አቀፍ ደረጃ “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ መልዕክት በአንድ ጀምበር የ800 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።
በመርሐ ግብሩ የኢፌዴሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ችግኝ በመትከል አሻራቸውን አሳርፈዋል። ፕሬዝዳንቱ ባስተላለፉት መልዕክት የኢትዮጵያ ጫካዎች በተፈጥሮ ጸጋ የተቸሩን እንጂ ተነሳሽነታችን አናሳ ነበሩ ብለዋል።
በዚህም ከድርቅ እና በረሃማነት ጋር በተያያዘ ብዙ ዋጋ ከፍለንበታል ነው ያሉት። ይህንን ታሪክ ለማድረግ የተወጠነው የአረንጓዴ አሻራ ውጤታማ ተግባራት እየተከናወኑበት መኾኑንም ገልጸዋል።
“የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ባለፉት ዓመታት ተግባራዊ መኾኑ የምናልመው ሁሉ ዕውን የኾኑበት ዓመታት ናቸው” ብለዋል ፕሬዝዳንቱ።
የዘንድሮው መርሐ ግብርም ከፍተኛ መኾኑን ገልጸዋል።
ዘጋቢ:- አሰፋ ልጥገበው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous article“ችግኝ መትከል ሕልውናን መታደግ እና መጠበቅ ነው”
Next articleየአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ ግብር የእስካኹን እውነታዎች