
በሀገር አቀፍ ደረጃ “ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ መልዕክት በአንድ ጀምበር የ800 ሚሊዮን ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር እየተካሄደ ነው።
በመርሐ ግብሩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ችግኝ በመትከል አሻራቸውን አስቀምጠዋል። ከንቲባዋ በዚህ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት “አረንጓዴ አሻራ የዘመናችን የትውልዱ አሻራ ነው” ብለዋል።
ዛሬ እየተከልን ያለነው የነገውን ጥላ፣ ውበት፣ ልምላሜእና ምግብ ነው ብለዋል። በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በመርሐ ግብሩ በርካታ ችግኞችን ለመትከል በጋራ ርብርብ እየተደረገ መኾኑንም ገልጸዋል።
መትከል ብቻ ሳይኾን መንከባከብ እና መጠበቅ ከሁሉም አካላት የሚጠበቅ ኀላፊነት መኾኑንም መልዕክት አስተላልፈዋል።
#AMECO #greenlegacy #Ethiopia
ዘጋቢ:- አሰፋ ልጥገበው
