
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን የጭልጋ ወረዳ ነዋሪዎች ባለፉት ዓመታት የተተከሉ ችግኞችን በመንከባከባቸው ከአትክልት እና ፍራፍሬ ልማት እንዲሁም ከጥብቅ ደን ሀብት ተጠቃሚ መኾናቸውን ገልጸዋል።
አስተያየታቸውን ለአሚኮ የሰጡት የአካባቢው ነዋሪዎች እንዳሉት በተከናወኑ የተፈጥሮ ሀብት እንክብካቤ ሥራዎች የተጎዱ መሬቶች ማገገማቸውን እና ቀደም ሲል አንድ የነበረው የውኃ ምንጭ አሁን ወደ 15 በማደጉ መስኖ ለማልማት ዕድል መፍጠሩን ተናግረዋል።
የወረዳው ግብርና ጽሕፈት ቤት የተፈጥሮ ሀብት ልማት ቡድን መሪ ጌታው መለሰ በበኩላቸው በወረዳው ባለፉት ዓመታት ከተተከሉት ችግኞች ውስጥ ከ88በመቶ በላይ መጽደቃቸውን እና ማኅበረሰቡ ተግባሩን በባለቤትነት እየደገፈ መኾኑን ገልጸዋል።
ዘንድሮም ለምግብነት የሚውሉ፣ ለአፈር እና ውኃ ጥበቃ እንዲሁም ለደን ልማት የሚኾኑ ችግኞች ትኩረት ተሰጥቷቸው እየተተከሉ ይገኛሉ ነው ያሉት።
#AMECO #greenlegacy #Ethiopia
#ጎንደር #ሐምሌ_27_2018_ዓ_ም
ዘጋቢ:- መሠረት ባየ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
