“በአንድ ጀምበር ተስፋን እና ለትውልድ ተሻጋሪ አረንጓዴ ኢትዮጵያን እናውርስ”

2

 

“ተስፋን እንትከል”በሚል መሪ መልዕክት በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን የመትከል መርሐ ግብር በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማቱ እየተካሄደ ነው።

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዲኤታ ሀሠን መሀመድ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ልክ እንደ መሪ ቃሉ ሁሉ በአንድ ጀምበር ተስፋን ለትውልድ ተሻጋሪ አረንጓዴ ኢትዮጵያን የምናስቀጥልቀት ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም በመሬት መራቆት፤ በብዝሀ ሕይወት መቀነስ፤ በአፈር መሸርሸር እና በውኃ ሃብት ስትፈተን መቆየቷን ተናግረዋል።

ይህም በኢኮኖሚው፣ በግብርናው እና በኢንዱስትሪው ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ሲያሳድር እንደነበር ሚኒስትር ዲኤታው ገልጸዋል። ይህ ሁሉ ተጽዕኖ ቢኖርም ባለፉት ሰባት ዓመታት በተካሄዱ የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብሮች የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ፤ ለዜጎች የሥራ ዕድል ከመፍጠር እና ኢኮኖሚውን ከማሳደግ ባለፈ ለዓለም የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖ መውጫ መንገድ አርዓያ የሚኾን ሥራ ተሠርቷል ብለዋል።

ችግኞችን መትከል ብቻ ሳይኾን ተንከባክቦ ማጽደቅ ላይም ርብርብ ማድረግ ይገባል ነው ያሉት።

#AMECO #greenlegacy #Ethiopia

#አዲስ_አበባ #ሐምሌ_27_2018_ዓ_ም

ዘጋቢ፦ ቤተልሔም ሰለሞን

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleየርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ መልእክት፦
Next article“የአረንጓዴ አሻራ የዘመናችን የትውልዱ አሻራ” ከንቲባ አዳነች አቤቤ