የነገዋ ኢትዮጵያ ዛሬ ትገነባለች

12
የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከሌሎች አጋር ተቋማት ጋር በመኾን ጳጉሜን አምስት የነገው ቀንን እንደሚያከብር አስታውቋል።
ዕለቱን በተመለከተ መግለጫ የሰጡት የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጅ ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ (ዶ.ር) ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት ፖሊሲ እና ስትራቴጂ ቀርጻ በዲጂታሉ ዘርፍ ያላትን አበርክቶ ከፍ ለማድረግ ሥትሠራ መቆየቷን ገልጸዋል።
ወጣቶች እና ሀገር ተረካቢ ሕጻናት ሞቹ በኾነ ሁኔታ ለመኖር እና ለመሥራት የሚያስችላቸውን መንገድ ለመጥረግ እንደሚሠሩም ተናግረዋል።
ይህን እውን ለማድረግ ደግሞ ሁሉም ኢትዮጵያዊ በተሠማራበት የሥራ መስክ የነገዋን ኢትዮጵያ በማሰብ መሥራት እንዳለበት ተናግረዋል።
የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030ን መነሻ በማድረግ በሀገር ደረጃ በቴክኖሎጅው ዘርፍ በርካታ ሥራዎች መከናወናቸውን አስታውሰዋል። የነገው ቀን ሲከበርም የዲጂታል ሥራዎችን ለማስታወስ፣ ሥራዎቹን በመጎብኘት እና በፖናል ውይይት እንደሚከበር ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
✍️ ዘጋቢ:- ሰላማዊት ነጋ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleከሚዲያ ሥራው ባለፈ የማኅበራዊ ኀላፊነቱን እየተወጣ የሚገኘው አሚኮ