
የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳዳር ሽመልስ አብዲሳ በምሥራቅ ሸዋ ዞን ፈንታሌ ወረዳ ኢላላ ቀበሌ ችግኝ ተክለዋል።
በባለፉት ዓመታት በተከናወኑ የአረንጓዴ ዐሻራ ሥራዎች በርካታ ውጤቶች መገኘታቸውን አቶ ሽመልስ ገልጸዋል።
ከተገኙት ውጤቶች መካከል የክልሉ የደን ሽፋን ከነበረበት 17 በመቶ ወደ 29 በመቶ ማደጉን ተናግረዋል።
በሚቀጥሉት ዓመታትም የደን ሽፋኑን ወደ 40 በመቶ ለማሳደግ የተቀናጀ ሥራ እየተሰራ እንደሚገኝ የጠቆሙት ርዕሰ መሥተዳድሩ፤ የተተከሉት ችግኞች የአየር ንብረትን ከማሻሻል ባለፈ ለምርትና ምርታማነት ማደግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከታቸውን አብራርተዋል።
