ሳፋሪኮም በአማራ ክልል እና የርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ መልእክት

48

 

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የሳፋሪ ኮም ከፍተኛ መሪዎችን በጽሕፈት ቤታቸው አወያይተዋል።

ሳፋሪ ኮም በአማራ ክልል እያከናወናቸው የሚገኙትን የኔትዎርክ ተደራሽነት ሥራዎች፤ ተቋሙ እያከናወናቸው ያለው የማኅበራዊ ኀላፊነት ድጋፎች እና እያጋጠሙ ባሉ ችግሮች ዙሪያ ነው ውይይት ያካሄዱት።

የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ በዚህ ወቅት እንደተናገሩት ሳፋሪኮም በክልሉ የኮሙዩኒኬሽን ዘርፍ መስፋፋት ትልቅ አስተዋጽኦ እያደረገ ነው ብለዋል። በክልሉ የኮሙዩኒኬሽን ዘርፍ መስፋፋት የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም ገልጸዋል።

በቴክኖሎጂ ልማት ሥራዎችም አጠናክሮ መቀጠል እንደሚያስፈልግ አንስተዋል።

በተጨማሪም በማኅበራዊ ኀላፊነት ላይ እያደረጉት ያለውን አስተዋጽኦ አጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል። የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት እና ለመደገፍ የክልሉ መንግሥት በትኩረት እንደሚሠራም አንስተዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ ሳፋሪኮም በባሕር ዳር ከተማ ለተማሪዎች የመማሪያ ቁሳቁስ እና ለባሕር ዳር ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የሥልጠና ማሽኖችን ድጋፍ አድርጓል።

የሳፋሪኮም የውጭ ግንኙነት ኀላፊ አንዷለም አድማሴ በዚህ ወቅት እንደገለጹት ሳፋሪኮም በአማራ ክልል ሰፊ ኢንቨስትመንት እያከናወነ ይገኛል ብለዋል።

የማኅበራዊ ኀላፊነቱንም በአግባቡ እየተወጣ እንደሚገኝ ተናግረዋል። የክልሉ መንግሥት ለሳፋሪኮም እያደረገ ለሚገኘው ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል።

በርክክቡ መልዕክት ያስተላለፋት የባሕር ዳር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ከተማ አሥተዳደሩ ከሳፋሪኮም ጋር በትብብር እንደሚሠራ ገልጸዋል።

ከተባበርን የተለወጠ ዜጋ እንፈጥራለን ያሉት ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው ሳፋሪኮም ማኅበራዊ ኀላፊነቱን ለመወጣት እያደረገ ላለው አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።

#አሚኮ #ሳፋሪኮም #ኢትዮጵያ🇪🇹

#ባሕር_ዳር #ነሐሴ_29_2018_ዓ_ም

ዘጋቢ፦ አሰፋ ልጥገበው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleአካል ጉዳተኞችን ወደ ኋላ የሚያስቀራቸው አካል ጉዳታቸው ሳይኾን ምቹ ያልኾነ አካባቢ እና አግላይ አሠራር ነው።
Next articleየፈተና እና ምዘናዎች አገልግሎት በሊቦከምከም ወረዳ ከ20 ሚሊዮን ብር በላይ በኾነ በጀት የትምህርት ቤት ግንባታ አስጀመረ።