“ችግኝ ስንተክል አብሮነትን፣ ፍቅርን እና አንድነትንም እናጸናለን”

4
በደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር በ2018 የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ከ9 ነጥብ 7 ሚሊዮን በላይ ችግኞችን ለመትከል ወደ ተግባር ተገብቷል።
ዛሬም በአንድ ጀምበር ከ390 ሺህ በላይ ቸግኞችን የመትከል መርሐ ግብር እየተካሄደ ይገኛል።
የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ተሾመ ዋለ ችግኝ መትከል የተፈጥሮ ሚዛንን ለማስተካከል የማይተካ ሚና ይጫወታል ብለዋል።
ችግኝ ስንተክል አብሮነትን፣ ፍቅርን እና አንድነትን አብረን እናጸናለን ነው ያሉት። ለሀገር እድገት በጋራ አላማ እና ለላቀ ልማት በተባበረ ክንድ መሥራት እንደሚገባም መልዕክት አስተላልፈዋል።
የከተማ አሥተዳደሩ ግብርና መምሪያ ኀላፊ መለሰ ሙላት በአንድ ጀምበር ከ390 ሺህ በላይ የደን፣ የውበት እና ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞችን ለመትከል እየተሠራ ስለመኾኑ ገልጸዋል።
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous article“ሠራዊቱ ሀገር እና ሕዝብን ከመጠበቅ ባሻገር በሚንቀሳቀስባቸው አካባቢዎች ሁሉ በልማት ሥራዎች ላይ በንቃት እየተሳተፈ ነው” ሜጄር ጄኔራል ዘውዱ ሰጥአርጌ
Next article“በባለፉት ዓመታት በተከናወኑ የአረንጓዴ ዐሻራ ሥራዎች በርካታ ውጤቶች ተገኝተዋል” ርእሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ