“ሠራዊቱ ሀገር እና ሕዝብን ከመጠበቅ ባሻገር በሚንቀሳቀስባቸው አካባቢዎች ሁሉ በልማት ሥራዎች ላይ በንቃት እየተሳተፈ ነው” ሜጄር ጄኔራል ዘውዱ ሰጥአርጌ

3
የመከላከያ ሠራዊት አባላት እና መሪዎች በደሴ ከተማ በተካሄደው “የአንድ ጀምበር “የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር ላይ በመገኘት አሻራቸውን አኑረዋል።
በኢፌዲሪ የመከላከያ ሠራዊት የ11ኛ ዕዝ ምክትል አዛዥ ለኦፕሬሽናል ሜጄር ጄኔራል ዘውዱ ሰጥአርጌ እንደተናገሩት ሠራዊቱ ሀገር እና ሕዝብን ከመጠበቅ ባሻገር በሚንቀሳቀስባቸው አካባቢዎች ሁሉ በልማት ሥራዎች ላይ በንቃት እየተሳተፈ ነው።
በሀገር አቀፍ ደረጃ 800 ሚሊዮን ችግኞች በሚተከሉበት በዚህ መርሐ ግብር ላይ በመሳተፋቸው ደስተኛ መኾናቸውን የገለጹት ሜጄር ጄኔራሉ የተተከሉት ችግኞች ለመጭው ትውልድ የሚተርፉ በመኾናቸው ሕዝቡ አስፈላጊውን እንክብካቤ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።
ዘጋቢ:- አሊ ይመር
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleየተተከሉ ችግኞች ለወጣቶች የሥራ ዕድል እየፈጠሩ ነው።
Next article“ችግኝ ስንተክል አብሮነትን፣ ፍቅርን እና አንድነትንም እናጸናለን”