ጎንደር ከተማ ከ370 ሺህ በላይ ችግኞችን በአንድ ጀምበር እየተከለች ነው።

3
ኢትዮጵያ በየዓመቱ እያካሄደች የምትገኘው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር ዛሬም ትኩረት እንደተሰጠው ነው።
በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማም ተፈጥሮን ለመታደግ ያለመው እና የፍራፍሬ ችግኞችን በመትከል የምግብ ዋስትናን ለማሳደግ አላማ ያደረገው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር እየተካሄደ ይገኛል።
በአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ በርካታ የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች በንቃት እየተሳተፉ ነው።
ከ370 ሺህ በላይ ችግኞች በዚህ የአንድ ጀምበር መርሐ ግብር እንደሚተከሉ የተናገሩት የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ግብርና መምሪያ ኀላፊ አበራ አደባ ናቸው።
እየተተከሉ ካሉ ችግኞች ውስጥ ከ11 ሺህ በላይ የሚኾኑት የፍራፍሬ ችግኞች ናቸው ብለዋል። በ15 የችግኝ መትከያ ቦታወች 64 ሄክታር የሚሸፍን መሬት በመርሐ ግብሩ እንደሚከናወንም መምሪያው አስታውቋል።
ዘጋቢ፦ ማርታ አዱኛ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleየአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ “የአንድ ጀምበር” የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አሻራቸውን አሳረፉ።
Next articleየተተከሉ ችግኞች ለወጣቶች የሥራ ዕድል እየፈጠሩ ነው።