የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ “የአንድ ጀምበር” የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አሻራቸውን አሳረፉ።

3
የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ የ800 ሚሊዮን “የአንድ ጀምበር” ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ ተገኝተው አሻራቸውን አሳርፈዋል።
ከርእሰ መሥተዳድሩ በተጨማሪ ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች፤ የዞን፣ የወረዳ ኀላፊዎች እና የአካባቢው ማኅበረሰብ ተገኝተዋል።
በችግኝ ተከላው ለኢኮኖሚያዊ እና ለደን ጥበቃ የሚያገለግሉ የተለያዩ ችግኞች እየተተከሉ ነው።
በአማራ ክልል “በአንድ ጀምበር” 327 ሚሊዮን በላይ ችግኝ በ65 ሺህ 900 ሄክታር መሬት ላይ እንደሚተከል የክልሉ ግብርና ቢሮ መረጃ ያመለክታል።
ዘጋቢ:- ያየህ ፈንቴ
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
Previous articleበሰሜን ጎንደር ዞን በአንድ ቀን ጀምበር የችግኝ ተከላ ከ3 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ችግኝ ለመትከል ኅብረተሰቡ እየተረባረበ ነው።
Next articleጎንደር ከተማ ከ370 ሺህ በላይ ችግኞችን በአንድ ጀምበር እየተከለች ነው።