በሰሜን ጎንደር ዞን በአንድ ቀን ጀምበር የችግኝ ተከላ ከ3 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ችግኝ ለመትከል ኅብረተሰቡ እየተረባረበ ነው።

5

 

“ተስፋን እንትከል” በሚል መሪ መልዕክት በአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በሰሜን ጎንደር ዞን ደባርቅ ከተማ እየተካሄደ ነው።

በተከላ መርሐ ግብሩ የሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት እና የአካባቢው ማኅበረሰብ እየተሳተፉ ይገኛሉ።

በአንድ ጀምበር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ በዞኑ ከ3 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ችግኝ ለመትከል መታቀዱ ተገልጿል።

በመርሐ ግብሩም ከ119 ሺህ በላይ ማኅበረሰብ በንቅናቄ ይሳተፋል ተብሎ ይጠበቃል።

የዞኑ ግብርና መምሪያ ምክትል ኀላፊ ፋሲካ መረሳ በዞኑ ከ45 ሚሊዮን በላይ ችግኞች ለመትከል ታቅዶ እስካሁን በተከናዎኑ ተግባራት ከ25 ሚሊዮን በላይ ችግኞች መተከላቸውን ገልጸዋል።

ከ500 ሺህ በላይ የአትክልት እና ፍራፍሬ ችግኞች እንደሚተከሉም ነው የጠቆሙት።

#AMECO #greenlegacy #Ethiopia

#ደባርቅ #ሐምሌ_27_2018_ዓ_ም

ዘጋቢ:- ደረጀ ደርበው

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article🌿 800 ሚሊዮን ተስፋዎች በአንድ ጀምበር!
Next articleየአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ “የአንድ ጀምበር” የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አሻራቸውን አሳረፉ።