🌿 800 ሚሊዮን ተስፋዎች በአንድ ጀምበር!

4

 

​የኢትዮጵያውያን ታሪካዊ የአረንጓዴ ዐሻራ ክንውን በይፋ ተጀምሯል!

​ለተጎዳችው ምድር ሕይወትን ለመመለስና ለቀጣዩ ትውልድ አረንጓዴ ነገን ለማስረከብ ያለመው “ተስፋን እንትከል” ታሪካዊ ሀገራዊ የመትከል መርሐ ግብር ዛሬ በመላው ሀገሪቱ በይፋ መጀመሩን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር እናትዓለም መለሰ አስታውቀዋል።

​በአንድ ጀምበር 800 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል የተያዘው ይህ ታላቅ ግብ፣ በዘንድሮው የክረምት ወቅት በአጠቃላይ የሚተከለው የ8 ቢሊዮን ችግኞች ዕቅድ ዋነኛ አካል ነው።

​ኢትዮጵያውያን በመደመር ዕሳቤ በአንድነት ሆነው ለምድር የሚሰጡትን አደራ መሬትም በተራዋ በእጥፍ እንደምትመልስ የገለጹት ሚኒስትሯ፤ እስከ ምሽቱ 12 ሰዓት ድረስ እያንዳንዱ የኅብረተሰብ ክፍል በነቃ ተሳትፎ ታሪክ መስራቱን እንዲቀጥል ጥሪ አቅርበዋል።

​ዛሬ የምንተክለው ችግኝ፤ የነገው የምድራችን ተስፋ ነው! 🌱✨
​#አረንጓዴ_ዐሻራ #ኑ_ተስፋን_እንትከል #ኢትዮጵያ #GreenLegacy #Ethiopia

Previous articleቻይና በአረንጓዴ ግንብ፣ ኢትዮጵያ ደግሞ በአረንጓዴ አሻራ የምድርን ጤና ጠብቀዋል።