“የሀገር መከላከያ ሠራዊት በችግር ጊዜ ሁሉ ከሕዝብ ጎን በመኖሩ ትልቅ ኩራት ይሰማናል” የመካነ ኢየሱስ ከተማ አሥተዳደር

13

 

የሀገር መከላከያ ሠራዊት ምሥራቅ ዕዝ ኮር ስታፍ እና የአንድ ክፍለ ጦር ስታፍ አባላት በደቡብ ጎንደር ዞን መካነ ኢየሱስ ከተማ አሥተዳደር ውስጥ በጎርፍ አደጋ ቤተሰቦቻቸውን ላጡ ህጻናት የ24 ሺህ 100 ብር ድጋፍ አድርገዋል።

የሁለት ህፃናት እናት እና አባት እንዲሁም ወንድማቸውን ጨምሮ በጎርፍ አደጋ ሕይወታቸውን በማጣታቸዉ ሠራዊቱ ከኪሱ በማዋጣት ነዉ የገንዘብ ድጋፋን ያደረጉት።

የኮር ምክትል አዛዥ ኮሎኔል ልጅዓለም ምትኩ እና የክፍለ ጦር አዛዥ ሌተናል ኮሎኔል ምሥራቅ መንበር ለቤተሰቦቻቸው መፀናናትን ተመኝተው “ይህ እኛ የምንደግፋቸው ድጋፍ ትንሽ ቢሆንም ልጆቹ ልጆቻችን ናቸው ብለን በሠራዊታችን ተነሳሽነት ድጋፍ አድርገናል” ብለዋል።

የመካነ ኢየሱስ ከተማ ከንቲባ ፀጋይ አበራ የኢፌዴሪ ሀገር መከላከያ ሠራዊት በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በደቡብ ጎንደር ዞን እስቴ ወረዳ መካነ ኢየሱስ ከተማ ዙሪያ ላይ ግዳጅ እየተወጣ ባለበት ቀጣና በከተማ አሥተዳደሩ ነዋሪ የኾኑ ሦስት ቤተሰቦቻቸውን በአንድ ጊዜ ላጡት ህፃናት ላደረገው ድጋፍ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል። “ሠራዊቱ በችግር ጊዜ ሁሉ ከሕዝብ ጎን በመኖሩ ትልቅ ኩራት ይሰማናል” ብለዋል።

ዘገባው የምስራቅ ዕዝ ነው።

#አሚኮ #defencenews #Ethiopia
#ባሕር ዳር ሐምሌ 26/2018 ዓ.ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleበአማራ ክልል በ14 ቢሊዮን ብር ወጭ በ1 ሺህ 408 ፕሮጀክቶች ላይ የመልሶ ግንባታ ሥራ ተከናውኗል።
Next article🌳 አረንጓዴ አሻራ – የኢትዮጵያ የተስፋ ትንፋሽ፣ የትውልድ አደራ እና የ56 ቢሊዮን ችግኞች ታሪካዊ ጉዞ