
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ 15ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል እና 18ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን አካሂዷል። ጉባኤው ሀገራዊ እና ማኅበራዊ ኀላፊነቱን ሲወጣ መቆየቱን የተናገሩት የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ዋና ጸሐፊ ሊቀ ትጉኃን ቀሲስ ታጋይ ታደለ ናቸው።
ጉባኤው በሀገሪቱ ሰላም እንዲሰፍን የበኩሉን አስተዋጽኦ አበርክቷልም ብለዋል፡፡
ችግሮችን ለመፍታት በጋራ መሥራት አማራጭ የሌለው መፍትሔ መኾኑ በመታመኑ የሃይማኖት አባቶች በጋራ እየሠሩ መኾናቸውን ጠቁመዋል፡፡
ጉባኤው በ15 ዓመታት ጉዞው ሕዝባዊ ኀላፊነቱን በአግባቡ እየተወጣ መጥቷል፤ በዚህም ሀገር አቀፍ እና ዓለም አቀፍ የሰላም ጉባኤዎችን በማዘጋጀት ውጤት ተመዝግቧል ብለዋል።
በቀጣይም ጉባኤው ለሀገር እና ለሕዝብ ጥቅም በትኩረት ይሠራልም ነው ያሉት።
ዘጋቢ: ራሔል ደምሰው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
