
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ 15ኛ ዓመት የምስረታ በዓል እና 18ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔውን አካሂዷል።
በጉባዔው ላይ የተገኙት የሰላም ሚኒስትሩ መሐመድ እድሪስ ጉባዔው በዓመታት ጉዞው ውስጥ የሃይማኖት ተቋማትን በማስተባበር የሀገሪቱን አንድነት እና አጋርነት በመደገፍ ውጤታማ የኾኑ ተግባራትን ሠርቷል ብለዋል።
ሀገሪቱ የምታከናውናቸውን የሰላም አጀንዳዎች ሲደግፍ የቆየ መኾኑን በሀገራዊ ምክክሩ ላይ ያደረገው ተሳትፎ ማሳያ እንደኾነም ገልጸዋል።
በቀጣይ ጉባዔው ሰላም ሚኒስቴር የሚተገብራቸውን የሰላም እና የአብሮነት ጉዞዎች በመደገፍ እና ከልዩነት ይልቅ የጋራ ጉዳዮች ላይ ትኩረት አድርጎ እንዲሠራም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ዘጋቢ፦ ራሔል ደምሰው
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
