በአማራ ክልል በ14 ቢሊዮን ብር ወጭ በ1 ሺህ 408 ፕሮጀክቶች ላይ የመልሶ ግንባታ ሥራ ተከናውኗል።

1

 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ (ዶ.ር) ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር ባደረጉት ቆይታ በሰሜኑ ጦርነት ጉዳት የደረሰባቸውን የአማራ ክልል አካባቢዎች መልሶ ከማልማት አኳያ በተከናወኑ ተግባራት ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአማራ ክልል 1 ሺህ 408 ገደማ ፕሮጀክቶች 14 ቢሊዮን ብር ወጥቶባቸው በመልሶ ግንባታ ተከናውነዋል ብለዋል። 459 ትምህርት ቤቶች፤ 210 ጤና ተቋማት፤ 358 የውኃ ተቋማት፤ 15 ከፍተኛ የኀይል ማከፋፈያ ተቋማት እና ሌሎችም ተቋማት መልሰው መገንባታቸውን ጠቅሰዋል።

የተጎዱ እና የተዘረፉ የኮምቦልቻ የኢንዱስትሪ ፓርክ እና የግለሰብ እንዱስትሪዎች፤ መልሰው ሥራ እንዲጀምሩ መደረጋቸውን አንስተዋል። የግል ባንኮችን ጨምሮ ከ4 ቢሊዮን በላይ ብር ተዘርፈው እንደነበርም ገልጸዋል። ይህንን መንግሥት ተክቶ እና ገንዘባቸውን አግኝተው ሥራ እንዲጀምሩ መደረጉን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

ተፋናቃዮችን ወደቀያቸው በመመለስም ሥራ መሠራቱን ጠቁመዋል። በጦርነት የተሳተፉ አካላት ከፊሉ ወደ መደበኛ ኑሮው እንዲመለስ፤ ከፊሉ ወደ መንግሥት የጸጥታ ኀይል እና ወደ ነበረ ሥራው እንዲገባና እንዲቋቋም የማድረግ ሥራ መከናወኑንም አብራርተዋል።

በሰዎች፣ በመንግሥት እና በግል ተቋማት እና በንግድ ድርጅቶች ላይ ሰፋፊ የመልሶ ግንባታ እና መልሶ ማቋቋም ሥራ ተሠርቷል ነው ያሉት።

#Ameco #መልሶማቋቋም #Ethiopia

በአድኖ ማርቆስ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article“መፈናቀልን እናስቀራለን ያሉ ኀይሎች አሁን ሰው ከቤቱ ወጥቶ መግባት እንዳይችል አድርገዋል”ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር)