
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከአሚኮ ጋር በነበራቸው ቆይታ በአማራ ክልል ወደ ጫካ የገቡት ኀይሎች ምክንያታቸው እና አሁን እያደረጉት ያለው የማይገናኝ ነው ብለዋል።
መፈናቀልን እናስቀራለን የሚል ምክንያት ያቀርቡ የነበሩት እነዚህ ኀይሎች አሁን ሰው ከቤቱ ወጥቶ መግባት እንዳይችል አድርገዋል ነው ያሉት።
የሕዝቡ ሀብት ንብረት የሚዘረፍበት፣ አዛውንቶች የሚገደሉበት፣ መምህራን የሚታገቱበት፣ ትምህርት ለማስተማር የሚቸገሩበት ሁኔታ መፈጠሩንም አንስተዋል።
በዚህ ጉዳይ የአማራ ሕዝብ ብልህ ሕዝብ ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን በጥልቀት እና በስክነት ቢገመግም ፍሬ ነገሩን ለማግኘት አይቸገርም ብለዋል።
ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር እያደረጉት ያለው ያልተቀደሰ ጥምረት በየትኛውም መንገድ ጥፋት እንጂ ውጤት አያመጣም ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
የአማራን ሕዝብ እንደ ሕዝብ በጠላትነት ፈርጆ በሰነድ አስቀምጦ በሀሰት ትርክት ሲታገል ከነበረ ኀይል ጋር መተባበር ጥቅሙ እና ጉዳቱ ምን ሊኾን እንደሚችል ማንም የሚገምተው ነው ብለዋል።
ኢትዮጵያን የጂኦግራፊ እስረኛ ካደረጉ ኀይሎች ጋር መተባበር በታሪክ ያለፍንበት የታሪክ ጠባሳን መድገም መሆኑን አስገንዝበዋል። እነዚህ ኀይሎች ከትናትናው ጥፋት ሊማሩ ይገባቸዋል ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ።
#Ethiopia #AmharaRegion #Ameco #AbiyAhmed #PeaceBuilding #CurrentAffairs
#ባሕር_ዳር #ሐምሌ_25_2018_ዓ_ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
