የመምህራን እና የትምህርት ቤት መሪዎችን አቅም የማጎልበት ሥራ እየተሠራ ነው።

8

 

ከ1ሺህ 500 በላይ መምህራንን እና የትምህርት ቤት መሪዎችን አቅም ለማጎልበት የሚያግዝ ሥልጠና በደሴ ከተማ መሰጠት ተጀምሯል።

የሥልጠና መርሐግብሩ በከፍተኛ የክልሉ የሥራ ኀላፊዎች የሚመራ ሲኾን የመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራንን እና መሪዎችን የሚያቅፍ መኾኑም በመድረኩ ተመላክቷል።

የአማራ ክልል መንግሥት ለትምህርት ዘርፉ በሰጠው ልዩ ትኩረት የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል የመምህራን እና የትምህርት ቤት መሪዎችን አቅም የማጎልበት ሥራ እየሠራ መኾኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አመላክቷል።

ለ2ኛ ዙር የሚሰጠው ሥልጠና በመካከለኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለሚገኙ መምህራን እና መሪዎች እንደኾነም ታውቋል።

ሥልጠናው ለ15 ቀናት የሚሰጥ ሲኾን በንድፈ ሀሳብ እና በተግባር ላይ ያተኮረ ስለመኾኑ የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ኀላፊ ጥላሁን ወርቅነህ በበይነ መረብ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግራቸው ጠቅሰዋል።

በትምህርት ዘርፉ አካባቢ የሚታየውን የሰው ኀይል ጥራት፣ የተነሳሽነት እና የብቃት ችግሮችን ሥልጠናው እንደሚያቃልልም ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

ባለፈው ዓመት ከ43ሺህ በላይ ለሚኾኑ መምህራን እና የትምህርት መሪዎች ሥልጠና የተሰጠ ሲኾን
በዚህ ዓመትም ከ10ሺህ በላይ ለሚኾኑ መምህራን እና የትምህርት መሪዎች ሥልጠናው እንደሚሰጥ ተጠቁሟል።

#አሚኮ #ትምህርት #አማራክልል_ኢትዮጵያ

#ደሴ #ሐምሌ_25_2018_ዓ_ም

ዘጋቢ፡-መሃመድ በቀለ

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous articleየቁስል ማከሚያ፤ የጋራ መግባቢያ እና የነገዋ ሀገር ግንባታ ምዕራፍ!
Next article🚫 ለሥልጣን ጥመኞች የሚከፈለው መስዋዕትነት እስከ መቼ