“በሀረር የዜጎችን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ እየተሠራ ነው” አቶ ሙክታር ሳሊህ

5

 

በሀረሪ ክልል በ2019 በጀት ዓመት የዜጎች የመኖሪያ ቤት ችግርን ለመቅረፍ እንደሚሠራ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር መዕረግ የሀረሪ ክልል ከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽን ቢሮ ኀላፊ ሙክታር ሳሊህ ገልጸዋል።

ቢሮው በተያዘው የ 2019 በጀት ዓመት የአገልግሎት አሰጣጡን በማጎልበት ለዜጎች ምቹ ከተማን ለመፍጠር እንደሚሠራ ነው ያብራሩት።

ቢሮው የማኅበረሰቡን ተጠቃሚነት ይበልጥ ለሚያረጋግጡ ተግባራት ትኩረት ሰጥቶ ይሠራልም ነው ያሉት።

በክልሉ ለመኖሪያ ቤት ግንባታ የሚውል 20 ሄክታር መሬት በማዘጋጀት በተለያዩ አማራጮች ዜጎችን የመኖሪያ ቤት ባለቤት ለማድረግ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሠራም ገልጸዋል።

የዜጎችን የመኖሪያ ቤት ችግር ለመቅረፍ የተያዘውን ዕቅድ በፍጥነት ተግባራዊ በማድረግ ዜጎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ርብርብ ይደረጋልም ብለዋል።

በሌላ በኩል የከተማ፣ ገጠር እና የሰፈሮችን ፕላን ሽፋን ለማሳደግ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሠራ እና የካዳስተር ሽፋንን ለማሳደግ ጥረት እንደሚደረግም ነው ያስገነዘቡት።

በተለይ የማኅበረሰቡን ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ በክልሉ የሚከናወኑ የአየር ማረፊያ፣ የኮሪደር ልማት ግንባታ አና ሌሎች ፕሮጀክቶች በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ ትኩረት ተሰጥቷል ብለዋል።

የአገልግሎት ተደራሽነትን በማሳደግም የዜጎችን የኑሮ ጥራት ለማሻሻል እና ዘላቂ የከተማ ልማትን ለማረጋገጥ ይሠራልም ብለዋል።

በተለይ የተቋሙን የአገልግሎት አሰጣጥ ይበልጥ በማዘመን ለዜጎች ፍትሐዊ፣ ፈጣን እና ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እንደሚሠራ ነው አቶ ሙክታር ሳሊህ የገለጹት።

#አሚኮ #የዜጎችን_ኑሮ_ማሻሻል #ሀረር_ኢትዮጵያ

#ባሕር_ዳር #ሐምሌ_25_2018_ዓ_ም

የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!

Previous article“የሀገር ግንባታ ዋልታዎች”
Next articleየቁስል ማከሚያ፤ የጋራ መግባቢያ እና የነገዋ ሀገር ግንባታ ምዕራፍ!