
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ጋር በነበራቸው ቆይታ ሰዎች በተለያየ ምክንያት ለውጡን በመደገፍ እና ባለመደገፍ ጎራቸውን ሊቀያይሩ እንደሚችሉ ተናግረዋል። በሦሥት ዋና ዋና ምክንያቶችም ጎራ መቀያየር ያጋጥማል ነው ያሉት።
✍️አንደኛው ለውጡ ሲመጣ የተሳሳተ ስሌት በነበራቸው ሰዎች መኖር መኾኑን ጠቅሰዋል። የሚሠራው ሥራ እኔ ባሰብኩት መንገድ መኾን አለበት ከተቻለ የምነግስ ካልተቻለ ደግሞ የማነግስ መኾን አለብኝ የሚል እምነት የተጋባባቸው ግለሰቦች ነበሩም ብለዋል። ብዙ ሰው ይሄን ለውጥ ያመጣሁት እኔ ነኝ ብሎ ማመኑንም አንስተዋል። እነዚህ ሰዎች ለውጡን ብዙ ሰዎች ዋጋ የከፈሉበት፣ በብዙ ድካም የመጣ፣ በጋራ የሚመራ እንጂ የግል ፍላጎት ለማሳካት የሚፈጸም አለመኾኑን ሲረዱ የጎራ ለውጥ አሳይተዋል ነው ያሉት። አንድን ለውጥ በራሰ መነጸር ብቻ በማየት ሌሎች ሰዎችን ማድመጥ ሲሳን ደግሞ ይሄ ችግር ያጋጥማል ብለዋል።
✍️ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ለእርካሽ ዓላማ የሚቃወሙ ሰዎች መኖራቸው መሆኑን ጠቅሰዋል። ከዩቲዩቭ ንግድ ጋር የሚያያዝ እና ወደ አንዳንድ ሀገሮች ለመጠጋት በሚደረግ ሙከራ ስድቦች እና መንቋሸሾች እንዲኖሩ አድርገዋል ብለዋል። ይህም አንዳንድ ሰዎች ወደ ኢትዮጵያ ሲመጡ የመጸጸት እና ተመልሰው ሲሄዱ ደግሞ የሚጻረሩ ሲኾኑ ተስተውለዋል ነው ያሉት።
✍️ሦሥተኛው ምክንያት በአንዳንድ ጉዳይ ላይ እውነተኛ ጥያቄ ያላቸው ሰዎች መኖር እንደኾነ ተናግረዋል። ላነሱት ጥያቄ በቂ ምላሽ ያላገኙ ሲመስላቸው እንደዚህ ዓይነት ስሜት ይፈጠራል፤ ይህም ” የእኛ ድክመት ያለበት ሊኾን ይችላል” ነው ያሉት።
እንዴት ይቀጥሉ? በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄም እውነተኛ ጥያቄ ያላቸው ይምጡና ቀርበው ይጠይቁ፣ አብረው ይሥሩ ነው ያሉት። ለውጥ ዳር ላይ ብቻ በመቆም አይሳካም ብለዋል።
በተሳሳተ መንገድ እና ስሌት የለውጡን ውጤት የገመቱ ሰዎች የኢትዮጵያን ነባራዊ ሁኔታ እና ዘመኑን መገንዘብ ያስፈልጋልም ነው ያሉት። ለውጥ የአንድ ሰሞን ድግስ አይደለም፤ በዛ ሂደት ውስጥ ብዙ ጉዳዮች ይቀያየራሉ፤ በወቅታዊ ችግር በመወላወል የሀገርን ጥቅም ማሳጣት ጥቅም የለውምም ብለዋል።
#አሚኮ #ወቅታዊ_ጉዳይ #ጠቅላይ_ሚኒስትር_ዐቢይ_አሕመድ #ባሕር_ዳር #ኢትዮጵያ #AMECO #PMABIYAHMED #PMAbiy #AmharaMediaCorporation #Ethiopia #BahirDar #CurrentNews
#ባሕር_ዳር፡ ሐምሌ 24/2018 ዓ.ም
የአሚኮ ዲጂታል ሚዲያ ቤተሰብ ይሁኑ!
